Tender Detail

Tender Details

  • Company የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ በአልትሜት ሞተርስ ገባ ብሎ የቀድሞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 45 01 82
  • Website
  • Deadline24 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-24 00:00:00
  • Categories Safety And Security , Machinery

የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ሴክተር ማዘጋጃ መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የእሳት አደጋ መኪናዎች ሥራ ማስጀመሪያ የተለያዩ መሳሪያዎች እና የግሪነሪ ቦታ ሳር ማጨጃ ማሸን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ሴክተር ማዘጋጃ መ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የእሳት አደጋ መኪናዎች ሥራ ማስጀመሪያ የተለያዩ መሳሪያዎች እና የግሪነሪ ቦታ ሳር ማጨጃ ማሸን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

በዚሁ መሠረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:30 ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ስንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሣብ ቁጥር 1064540111215 ገቢ በማድረግ ዲፖሲት ሲልፑን/ Deposit slip ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንፃ አንደኛ ፎቅ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክትር ክፍል በማቅረብ እና ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ሁለተኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የተጫራቾች ግዴታዎች

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም ኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ 200,000.00 ብር CPO (ሲፒኦ) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ግዴታ አለበት።
  5. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ብቻ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የመንግስት የሥራ ቀናት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንጻ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬከተር 2ተኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ጨረታው በ16ተኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አደራሽ ይከፈታል። እለቱ ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥሮች፡- 0114-70-93-00 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ሳሪስ በአልትሜት ሞተርስ ገባ ብሎ የቀድሞው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ

 

የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender

የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የልብስ ስፌት ስራ ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሚ...

READ MORE
Procurement of Machinery

READ MORE
NRC Ethiopia Tender for Security Guard Services in North Area Operations Under a Two-Year Framework...

READ MORE