Tender Detail

Tender Details

  • Company በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ
  • Address ድሬዳዋ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0910595368
  • Website
  • Deadline23 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security5,000.00
  • opening date2025-10-23 00:00:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ 2018 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ 2018 ዓ/ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች።

4ተኛ ሎት አራት መድሃኒት

1.1 ተጫራቾች በዘረፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

1.2 በመንግስት ግዥ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

1.3 ተጫራቾች የታከስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

1.4 ተጫራቾ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሠዓት ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል በጎሮ ጤና ጣቢያ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ አንደኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

1.5 መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5000/አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም (BI BOND) በጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

1.6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቬሎኘ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

1.7 የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኃላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

1.8 የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በፁሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት።ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

1.9 ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን እና _ ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

ማሳሰቢያ፦ ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማስረጃ፡- በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ

መደወል ይቻላል።025111456(0910595368)

በድሬዳዋ አስተዳደር ጎሮ ጤና ጣቢያ

Save Tender