Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-73-62-69
  • Website
  • Deadline27 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-27 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Water Construction , Water Well Drilling

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ መአድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ እንስታሌሽን በጅዳ ወረዳ ቀበሌዎች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ መአድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ እንስታሌሽን በጅዳ ወረዳ ቀበሌዎች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

የጅዳ ወረዳ ውሃ መአድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ ኢንስታሌሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስቆፈር እና ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም አስፈላጊውን የሰው ሀይል እና ማቴሪያል አሟልቶ ለማሰራት ፈቃደኛ የሆኑትን ሥራ ተቋሯጮችን ይጋብዛል።

በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. ድርጅቱ ለ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ክሊራንስ (Tax clearance) እና (Tin number) ቲን እና (Drilling license) እና በስራ ዘርፍ (Drilling well) 5 ደረጃ እና ከዚያ በላይ ያላው መሆን አለበት። እንዲሁም ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በውሃ ጉድጓድ (water well) ዘርፍ ያለው መሆን አለበት።
  2. ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ (ማለትም ከ2016-2017 ዓ.ም ድረስ) የሚያሳይ የስራ ልምድ (water well Drilling license) ከሚመለከተው አካል ላይ ማቅረብ አለበት። እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 5 እና ከዛ በላይ (1-5) የሚያሳይ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በውሃ ጉድጓድ ዘርፍ (water well Drilling license) ማቅረብ አለበት።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለውሃ ጉድጓድ water well ቁፋሮ የሚያገለግል ማሽን ያለው መሆኑን የሚያሳይ ሊብሬ (Libre) ያለው ወይም ውክልና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቹ የውሃውን water well 60 ሜትር ወደ ታች መቆፈር ያለበት ሆኖ እንደስፈላጊነቱ 10 ሜትር ጥልቀቱን መጨመር ወይም መቀነስ (60+10) ይችላል።
  6. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ የሚያገለግል ሁሉንም የማሽን አይነት ያለውና የድርጅቱን የሰው ሀይል እና የስራ ድርሻውን የሚገልፅ ፕሮፋየል ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ apron (well head) የሚያገለግሉ ሁሉንም ዕቃዎችን እና ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በራሱ ማቅረብ አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የአጅ ዋጋ እና የእቃ ዋጋ (material cost and labour cost) አንድ ላይ መሙላት አለባቸው።
  9. ተጫራቹ Well completion report and water test quality report ማቅረብ አለባቸው።
  10. ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ በካሽ፣ በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ለጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በማለት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
  11. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ እያንዳንዳቸው ዶክመንት ላይ ኦሪጅናል እና ኮፒ፣ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ እንዲሁም CPO በማለት በፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  12. አሸናፊው ድርጅት ለስራ ማስጀመሪያ ቅድመ ክፍያ (Advance payment) ለመውሰድ ከማኛውም ባንክ (unconditional bank guarantee) ማቅረብ አለበት።
  13. አሸናፊው ድርጅት ለስራው ክፍያ ሰነድ (payment certificate) በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ አለበት።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 14/02/2018 ዓ.ም ቀን ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  16. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 17/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡45 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  17. ጨረታው በቀን 17/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
  18. ተጫራቾች የተሟላ ሰነድ መግዛታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
  19. ከጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት በኋለ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  20. ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ስልክ ቁጥር፡- 011-6-73-62-69/ 011-6-73-61-12/ 011-6-73-63-28

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender