ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኃ.ተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ትራከር ፣ ሲኖትራክር ፣ ቮልቮ እና ተሳቢዎች እንዲሁም ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኃ.ተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ትራከር ፣ ሲኖትራክር ፣ ቮልቮ እና ተሳቢዎች እንዲሁም ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ይህንን ጨረታ እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከባድ ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች በሚገኙበት ኮምቦልቻ በሚገኘው የኩባንያው ማሰልጠኛ ተቋም እና አዳማ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመሄድ የገዙትን የጨረታ ሠነድ በማሳየት መኪኖችን ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የተሽከርካሪውን ጨረታ መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዱ ጋርበማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናቶች ዘወትር በስራ ሠዓት ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ጥቁር አባይ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኃ.የተ.የግል ማህበር አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ በኩባንያው ዋና መ/ቤት መዝገብ ቤት እንዲሁም አዳማ እና ባህር ዳር በኩባንያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋውን በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ኮምቦልቻ እና ባህር ዳር በሚገኘው የኩባንያው ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል ።
- የጨረታ መዝጊያው ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በስራ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች እና በቅርንጫፎች ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ላይ የሚከፈት እና የሚዘጋ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ከአሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንት/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በስምንት ቀን ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡
- ከተሽከረካሪዎች የስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ወጭዎችን ገዥ ይከፍላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች መኪናውን የሚረከበው ያሸነፈበትን ገንዘብ ከፍሎ ስሙን ካዞረና ስሙ የዞረ ለመሆኑም የዞረውን ሊብሬ ሲያቀርብ ብቻ ነው።
- በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-552-77-48 ወይም 011-557-38-24
ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
