የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1፡- ገልባጭ መኪናዎችን ለመከራትና በሎት 2- የተለያዩ ማሽነሪዎችን ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር እና ሎደር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ 001/2018
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል በሎት 1፡- ገልባጭ መኪናዎችን ለመከራትና በሎት 2- የተለያዩ ማሽነሪዎችን ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር እና ሎደር በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝር መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፊቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ «ኦርጅናል›› እና «ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 በማስገባት ባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው እስከ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ይሆናል። /ጨረታው በ15ኛ ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ። እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በቅድሜ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፤ ከጨረታ ደንብና መመሪያ በውጭ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግስት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም
በስልክ ቁጥር፡- 0474527941/0947527727 ደውለው ማነጋገር ይችላል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት
