የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው መንገድና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት ለሚያስጠግነው መንገድ የማሽን ኪራይ ተከራይቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፤ እንዲሁም ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት አዲስ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው መንገድና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት ለሚያስጠግነው መንገድ የማሽን ኪራይ ተከራይቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፤ እንዲሁም ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት አዲስ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳዳር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈለና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ።
- ቲን፤ ቲኦቲ፤ ወይም የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- እንዲሁም 2% CPO ከዋናው (Original Technical) ቴክኒካል ሰነድ በአንድ ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- በውሃ ስራ ላይ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ለመንገድ የማይመለስ 1000 (አንድ ሺ ብር) ፤ ለውሃ ጉድጓድ 500 (አምስት መቶ) ብር ለወረዳ ገቢዎች በመክፈል ከግዥ ክፍል መግዛት የሚችል፤
- Withholding Tax (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ።
- ተወዳደሪዎች የማሽኑን ስም፤ ሞዴል፣ ማሽኑ የተሰራበት ዓመተ ምህረት ፤ የማሽኑ ጉልበት፣ ብዛት፣ የግል ወይም ኪራይ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ኦርጂናል አንድ እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል ኦርጂናል፤ ፋይናንሽያል ኦርጂናል ፣ ቴክኒካል ኮፒ 1፣ ቴክኒካል ኮፒ 2፣ ፋይናንሽያል ኮፒ 2 በማለት ራስጌው ላይ በመፃፍ ሁሉም ፖስታ ላይ ስም፣ አድራሻ፣ የመንገድ መስመር በመጻፍ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ዋና ፖስታ ውስጥ ገብቶ ታሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከአንድ ጊዜ በላይ ለውድድር የሚቀረቡ 2% CPO ማስያዝ ይገደዳሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለይቶ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡
- Pommiቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል፡፡
- የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 2 በኋላ ለ21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ21ኛው ቀን በ6፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ሊከፈት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ለስራው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወጪ በራሱ የሚሸፈን ይሆናል።
- የምንከራየው ሰዓት: በሰዓት ወይም የሚቆፈረው ጉድጓድ ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 047-342-03-03
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
