በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤት አስፓልት ዳር የመንገድ መብራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለማዘጋጃ ቤት አስፓልት ዳር የመንገድ መብራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉና እንዲሁም የተ/እ/ታ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሊወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር ከዶዶላ ከተማ አስ/ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ፖስታው ታሽጎ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ሆኖ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች /ተወዳዳሪዎች/ ተወዳድረው አሸናፊ በሆኑበት እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ማጓጓዣ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ነገሮችን አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ5 ቀን ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ አድራሻ፣ ስም፣ ፊርማ ማህተምና ስልክ ቁጥር ማስፈር ይጠበቅባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ማንኛውንም ዕቃ ጥራታቸው በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያስገቡትን መረጃና ሰነድ የእኔ አይደለም ማለት አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ከሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች በገዙት ሰነድ ላይ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በተዘጋጀ ቦታ ላይ መሙላትና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ናሙና እንዲቀርብባቸው ከሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረቡትን ዕቃዎች የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
