ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉት የሕክምና ማዕከሎቹ አገልግሎት የሚውሉ የመኝታ ጨርቆችን (አንሶላ፣ አቡጀዲ፣ እና የፒጃማ ጨርቅ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Hamlin Fistula Ethiopia (ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ)
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዞን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላሉት የሕክምና ማዕከሎቹ አገልግሎት የሚውሉ የመኝታ ጨርቆችን (አንሶላ፣ አቡጀዲ፣ እና የፒጃማ ጨርቅ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር የአማርኛው ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /07/ ተከታታይ የሥራ ቀናት አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በመገኘት፣ የሚፈለጉትን የጨርቅ አይነቶች ናሙና በመመልከት፡ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ከፍለው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጨረታው ተወዳዳሪ ድርጅቶች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማክሰኞ መስከረም 13/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 በድርጅቱ የስብሰባ ማዕከል ይከፈታል።
. ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ .
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46-የውስጥ መስመር 139/182
