Tender Detail

Tender Details


በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአገልግሎት እና እቃ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

  1. በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአገልግሎት እና እቃ ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1. የመድረክ የዲኮር እና ሳወንድ ሲስተም አገልግሎት ግዥ

ሎት 2. የህትመት አገልግሎት ግዥ

ሎት 3. የጉልበት ስራ አገልግሎት ግዥ

ሎት 4. የካሜራ ሰርቨር እና LED ግዥ

በመሆኑም ተጫራቾች:-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።
  2. ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  4. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
  5. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡- 0115548264/0118-69-43-66

 

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

 

Save Tender