የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ 3Kg Carbon dioxide fire extinguisher ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/BM/131/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ 3Kg Carbon dioxide fire extinguisher ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃውን ዓይነት |
የፕሮጀከት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
|
ጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
3Kg Carbon dioxide fire extinguisher |
ጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀከት
|
DCE/BM/131/2025
|
ጰጉሜ 05/2017 ዓ.ም 4:00 ሰዓት
|
ጰጉሜ 05/2017 ዓ.ም 4:15 ሰዓት
|
50000.00 |
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስከር ወረቀት (ታክስ ከሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) 120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከኢዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው-ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከኢዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ ዐ114-42-22-70/71/72 E-mail አድራሻ Info@dce-et.com የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ. ቁ 0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
