Tender Detail

Tender Details


በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ፅ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አላቂ የቢሮ ዕቃ (እስቴሽነሪ) ፤የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ህትመት አገልግሎት የዲኮር ስራን ጨምሮ፣ የጥገና /የአይቲ/ አገልግሎት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ጌጣጌጥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ፅ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አላቂ የቢሮ ዕቃ (እስቴሽነሪ) ፤የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ህትመት አገልግሎት የዲኮር ስራን ጨምሮ፣ የጥገና /የአይቲ/ አገልግሎት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ጌጣጌጥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በሚሰጠው አገልግሎት ከመ/ቤቱ ጋር ውል ወስዶ በሚፈለገው ሰዓት ማቅረብ እና አገልግሎቱን መስጠት የሚችል፡፡
  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀን የካ ክፍለ ከተማ /ወረዳ 2 ፋ/ፅ/ቤት የጨረታ መመሪያ፣ የዕቃና አገልግሎት እስፔስፍኬሽን አጠቃሎ የያዘ የጨረታ ሰነድ በአካል መጥተው በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • አሸናፊ በሚሆኑበት እቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒዮ ማስያዝ የሚችል።
  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታተይ የስራ ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜ /የበዓል/ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በተመለከተ ደንብ ልብስ 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ) እስቴሽነሪ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) የፅዳት እቃ 34,000.00 (ሰላሳ አራት ሺህ) ትራንስፖርት 5,000 (አምስት ሺህ) ህትመት 5,000.00 (አምስት ሺህ) ጥገና አገልግሎት 3,000.00 (ሶስት ሺህ) ፣ የመኪና መለዋወጫ 5,000.00 (አምስት ሺህ) እና መስተንግዶ 3,000.00 (ሶስት ሺህ) CPO ብቻ ማስያዝ እንዳለባቸው እየገለፅን በድጋፍ ደብዳቤ ለምታመጡ ነጋዴዎች የምታስገቡት እቃ በሀገር ውስጥ ለሚመረት እቃዎች፣ ለትራንስፖርት፣ ለህትመትና ለጥገና እና ለመስተንግዶ አገልግሎት የሚናስተናግድ ሲሆን ከሃገር ውጪ ለሚመረቱ/ለሚገቡ ምርቶች በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግድ ነው፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡- ፈረንሳይ አደባባይ ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ የካ ክ/ከ ወረዳ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111548903 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ፋ/ጽ/ቤት

 

Save Tender