Tender Detail

Tender Details

  • Company የባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ ስራ ማህበር
  • Address በባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ በብሎክ 12 የቤት ቁጥር 2 በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912 01 76 24
  • Website
  • Deadline28 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-28 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

የባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ ስራ ማህበር የ2016 እና 2017 ዓ.ምን የማህበሩን ሂሳብ የተፈቀደላቸው የሒሳብ አዋቂዎችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል::

የባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ ስራ ማህበር


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ ስራ ማህበር የ2016 እና 2017 ዓ.ምን የማህበሩን ሂሳብ የተፈቀደላቸው የሒሳብ አዋቂዎችን አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቶች (ተጫራቾች) ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 - 6፡00 ከሰዓት ከ 7:30 - 11:00 እና ቅዳሜ ከ 2:30-6:00 በፖስታ የታሸገ የጨረታ ዶክመንታችሁን በባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ በብሎክ 12 የቤት ቁጥር 2 በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

ለመጫረት በምትመጡበት ጊዜ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች፡-

  1. የኅብረት ስራ ማህበራችንን ሂሳብ ለመመርመር ፈቃደኛ መሆንን (በቦታውና በሰአት ለመገኘት)
  2. ህጋዊ የሙያ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው ያላት፡፡
  3. ከ አንድ አመት በላይ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የቅርብ ጊዜ ኦዲት ያደረጋቸውን ቢያንስ 3 (ሶስት) ድርጅቶች ወይም ማህበራት ዝርዝር ማቅረብ የሚችል።
  5. በህብረት ስራ አዋጅ መሰረት ሂሳቡን መመርመር የሚችል መሆን አለበት፡፡
  6. የኦዲት ድርጅትዎ ቢመረጥ ለተጠቀሱት ዓመታት የኅ/ስራ ማህበራችን የሚጠየቀውን ክፍያ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በፊትና በኋላ የሚገልፅ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  7. የሪፖርቱን ቴርሚኖሎጂስ (Terminologies) በአማርኛ ተርጉሞ ለጠቅላላ ጉባኤ ሊይቀርብ የሚችል።
  8. የዘመኑን የሙያ ግብር ገብሮ ለመገበሩ ማስረጃ (clerance) ማቅረብ የሚችል፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10 (በአስረኛው) ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች (ተጫራቾች) ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ማህበሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 01 76 24 መደወል ትችላላችሁ።

 

የባሻ ወልዴ ችሎት የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የኅ/ ስራ ማህበር

 

Save Tender