የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ፈቃድ ባላችው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር የኦዲት ሥራ
የጨረታ ማስታወቂያ
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር ከየካቲት 01/2012 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ያለውን የማኅበሩ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሕጋዊ ፈቃድ ባላችው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ማኅበሩን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰ/ች።
- በሂሣብ ምርመራ /ኦዲት ተግባር ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት ፣ CV /የትምህርት ደረጃ/፣ የሥራ ልምድ ወዘተ ከእያንዳንዱ ባለሙያ ጋር የተያዘ /የተገባ/ የቅጥር ውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ።
- የበጀት ዓመት (ቶች) ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ሁለት በመቶ “በመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር” ስም ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያከናውኑትን ተግባር በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል።
- ከተቻለ ተጫራቾች ስለመልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሣብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድርጀቶች የተፃ ላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (ተመዝጋቢ ከሆነ) ፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት /ቲን እና ሌሎች ሕጋዊ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን በጀት ዓመት ኦዲት ሥራ፤ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትን የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ (ከነሐሴ 12/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 22/2017 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፤ ሳርቤት አካባቢ በሚገኘው መቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ግቢ፤ የማኅበሩ ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላትና በኤንቨሎፕ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር :- +251911901971/+251924241388 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመቻሬ ሜዳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማኅበር
