የምዕራብ ወለጋ ዞን ገ/ጽ/ቤት ለምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽ/ቤት በ2018 በአሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች ከእንጨት መሰንጠቂያ ጣቢያዎች ጣዉላ ለማጓጓዣ በከባድ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የግል ተሽከርካሪ ባለንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገ/ጽ/ቤት ለምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽ/ቤት በ2018 በአሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች ከእንጨት መሰንጠቂያ ጣቢያዎች ጣዉላ ለማጓጓዣ በከባድ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የግል ተሽከርካሪ ባለንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጫን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የጨረታ መስፈርቶችን የሚታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ‐ ተጋብዘዋል፡፡
-
በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
የ2017 ዓ/ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት (TIN) እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
-
ተጫራቾች የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው
-
ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 2% በተረጋገጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር( 200) ሁለት መቶ በመክፈል የግዥ ክፍል ከመ/ቤቱ(G+1) ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን አገልግሎት በሚያቀርቡት የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ እና በድርጅቱ ማህተም፣ ፊርማና ስም አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
-
የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራቀን፣ ከቀኑ በ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 (በስምንት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
-
ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ የሚፈለገው ቦታ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤
-
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577712547 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
-
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
