የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በቅምብቢት ወረዳ ስርላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር ግዥ በቅምብቢት ወረዳ ስርላሉ ባለ በጀት መ/ቤቶች የተለያዩ፡
- የጽህፈት መሳሪያ እና ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች
- የመኪናና የሞተር ጎማዎች
- የደንብ ልብስ
- የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤የተጨማሪ እሴት ታከስ “VAT 15%"ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታውን ሰነድ በቅምብቢት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 1000 በካሽ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ “CPO” ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይበመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ፦ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910118219 /0910 913798 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የቅምብቢት ወረዳ 7ንዘብ ጽ/ቤት
