አወሊያ የእርዳታና ልማት ድርጅት ስር ለሚገኘው የወሊሶ ህፃናት መንደር 120 ሜትር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራን ለማሰራት ይፈልጋል።
Awolia Relief and Development Organization (ARDO) (አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት)
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አወሊያ የእርዳታና ልማት ድርጅት ስር ለሚገኘው የወሊሶ ህፃናት መንደር 120 ሜትር የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራን ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ድርጅታችን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ በመስኩ ልምድ ያላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ ንፁህ የመጠጥ ውሃን የማውጣት ስራን ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለድርጅታችን ውሃ የማውጣት ስራ መስራት የሚፈልጉ ተጫራች ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
- የጨረታ ሰነዱን የድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ዋና ክፍል በአካል በመቅረብ የማደመሰስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 147C23000023 አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ስም በማስገባት ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ዋና ክፍል በአካል በመቅረብ የዋጋ ዝርዝር ማቅረብያ ቅፅ (Bill of Quantity) ላይ ለድርጅቱ ስራውን የሚሰሩበትን ዋጋ በተናጠልና በጥቅል ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ትክክለኛ ስማችሁንና አድራሻችሁን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመፈረም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚሰሩት ስራ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሐምሌ 30/2017 ዓ.ም ነሀሴ 08/12/2017 ዓ.ም (5 ተከታታይ የስራ ቀናት) ከጠዋቱ 6:00 ሰአት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ሰኞ 8:00 በድርጅቱ የጨረታ ኮሚቴ ሙሉ አባላት በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ስራውን መጀመር ይኖርባቸዋል። ሆኖም በተቀመጠው በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተድርጎ እድሉ ለሁለተኛ አሸናፊው የሚሠጥ ይሆናል።
- ቦታው አዲስ አበባ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ከጀኔራል ዊንጌት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አለፍ ብሎ በሚገኘው ልዩ ቦታው አወሊያ ዋና መስሪያ ቤት ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0112708158 0112707916 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት!
