በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥው ዓይነት
ሎት 1: -የፅህፈት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የት/ ት አላቂ ዕቃዎች እና ለመዋለ ህፃናት የሚያገለግሉ የት/ት ዕቃዎች እንዲሁም አጋዥ መፅሐፎች የስፖርት ትጥቅ እና ለስፖርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ህትመት እና የጥገና ዕቃዎች ፣ የመጀመሪያ የህከምና መርጃ እና የቤተ- ሙከራ የሚያስፈልጉ Chemicals
ሎት2፡-የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3፡- የደንብ ልብስና ማሰፊያ
ሎት4 - ቋሚ ዕቃ እና ኤሌክትሮኒክስ
ሎት5- ሜንቴናንስ የኮምፒዩተር እና የፕሪንተር ማባዣና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና ፤የኤሌክትሪክ መስመር የተለያዩ ብልሽት ጥገና ፣ የውሃ መስመር ብልሽት ጥገና በአጠቃላይ ሁለገብ የሆነ የአገልግሎት ሠራተኛ ሎት 6 ለስልጠና መስተንግዶ ከላይ በተጠቀሰው መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአገር ውስጥ ገቢ እና የዘመኑ ግብርአጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና በአቅራቢዎች ላይ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ከላይ ከሎት 1-4 በተዘረዘረው መሰረት ሁሉም ሎት እያንዳንዳቸው ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ሲሆን 5 እና 6 ደግሞ በ200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በቂ/ክ/ከ/ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤትቢሮ ቁ 002/5 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሎት በተዘረዘረው መሰረት ከሎትı–4 እያንዳንዳቸው ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር / ሲሆን ሎት 5 እና 6 ደግሞ ብር 1500.00 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤትቢሮ ቁ 002/5) ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በቀረበው ናሙና መሠረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
- ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ለት/ቤቱ ሲያስረከቡና የቀረበው ዕቃ ጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
- ጨረታው በተዘጋ ማግስት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት 11/2017 ዓ.ም በሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/ አብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ የመ/ደ/ት/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 002/5 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ከላይ ከሎት 1-3 የተዘረዘሩት ዕቃዎች ናሙና ያስፈልጋቸዋል ሎት 4 ደግሞ በስዕል የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- ኦሎምፒያ የትራፊክ መብራቱ ጋ በዴይሎክስ ፈርኒቸር ገባ ብሎ አድማስ ኮሌጅ ዝቅ ብሎ ስልክ 0115510765 /0115579925 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወ/01 የአብዮት እርምጃ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከስኛ ደ/ት/ቤት
