Tender Detail

Tender Details


የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት አንድ፣ በሎት ሁለት እና በሎት ሶስት የተዘረዘሩት የተለያዩ የስራ አይነቶች፣ ጥገና እና ሰርቪስ ሥራዎችን ለማሠራትና ለማስጠገን በወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ የጨረታ አፈፃፀም መመሪያ

  • ሎት አንድ፡- የብረት በርና መስኮት ጥገና ሥራ፣ የዴስክ ጥገና ሥራ፣ የአዳራሽ ኮርኒስ ሥራ በማይካ፣ የመማሪያ ክፍል ኮርኒስ ሥራ፣ የከርቭ ስቶን ሥራ፣ የውሃ ቀለም ቅብ ሥራ፣ የክፍል ሥራ በቆርቆሮ፣ የብረት ቀለም ቅብ ሥራ፣ የውሃ ማውረጃ (Down pipe) ሥራ፣ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ሥራ፣ የቧንቧ ጡቶች ጥገና ሥራ፣ የመደርደሪያ ሥራ ለእቃ ማስቀመጫ (መደርደሪያ)፣ የአርማታና ሊሾ ሥራ፣ የድጋፍ ግንብ ሥራ፣ ሴራሚክ የማንጠፍ ሥራ፣ ቴራዞ የማንጠፍ ሥራ እና የግሪል ሥራ፣
  • ሎት ሁለት፡- የማባዣ ማሽን፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ ሲስተም ዩኒት፣ ጄኔሬተር ጥገና እና ሰርቪስ 
  • ሎት ሶስት፡- የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት የተለያዩ ቦታዎች እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል፡፡
  1.   ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኦኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት የታደሰ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ቁጥር 34 የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ መረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል፡፡
  3. ጨረታውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 10,200 ለሎት ሁለት ብር 2,500 ለሎት ሶስት ብር 2,000 CPO በመሥሪያቤቱ ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ የሰነዱ ገፅ ላይ በማኖር በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከሥራ ሂደቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በጠቅላላው ባሸነፈው ዋጋ 10% የሚመለስ በመሥሪያ ቤታችን ስም CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  7. ለሎት 3 ተወዳዳሪ ብቻ ማሟላት የሚገባውን ሰነድ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆነ የሚበረታታ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንሲሆን ይህን ማቅረብ ካልተቻለ በምትኩ ቲኦቲ (TOT) ከፋይ መሆን አለበት
  8. በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  9.  የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  10.  የመጫረቻ ሰነድ የማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ1ዐኛ ቀን እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ10ኛ ቀን 9፡00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የት/ት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11.  የመ/ቤቱ የዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ /የቴክኒክ ኮሚቴ/ ለሥራው የሚያቀርቡትን የዕቃዎቹን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል፡፡
  12.  የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ድርጅቶች/ ማሸነፍ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
  13.  ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14.  ማንኛውም ተጫራች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ቅሬታ ካለው ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቅሬታውን በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል፡፡
  15.  ማንኛውም ተጫራች ከዚህ መመሪያ ውጪ ሙስናና ከሙስና ጋር የተያያዙ ድርጊቶችን ቢፈፅም ወይም በህገ ወጥ መንገድ ለማሸነፍ ቢሞክር ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል ያስያዘውም ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡
  16.  በመሆኑም በኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገጉትን የሚያከብር መሆኑን በማረጋገጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ሙስና ላለመፈፀም ቃል የሚገባበትን ቅፅ በተጫራቹ ተሞልቶና ተፈርሞ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  17.  በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተገለፀለት አካል ወይም ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ (ቀናት) ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
  18.  የኤሌክትሮኒከስ ጥገና የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊ የሆነውን እቃ እንዲያቀርብ ሲታዘዝ በገበያው ዋጋ መሰረት ማስገባትና መጠገንም ሆነ መሥራት ይኖርበታል፡፡
  19.  ከላይ በተገለፀው መሰረት እያንዳንዱን ጥገና የሚሠራው አሸናፊ ድርጅት ለተጠገነው ዋስትና መስጠት ይኖርበታል፡፡
  20.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251 118 35 74 84/+251 118 35 74 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ-ከርስቲያን መግቢያ (ቀራንዮ አደባባይ)

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender