Tender Detail

Tender Details

  • Company TESFA BERHAN CHILD AND FAMILY DEVELOPMENT ORGANIZATION
  • Address D/Birhan, Ethiopia, Phone: 0961140705
  • Websitehttps://tesfab.org/
  • Deadline12 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineReporter
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1%
  • opening date2025-08-12 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Food And Beverage

ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከቻይልድፈንድ ጋር በመተባበርበትግራይ ክልል፤ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ ለሚተገብረው ፕሮጀክት የሚከተሉትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

TESFA BERHAN CHILD AND FAMILY DEVELOPMENT ORGANIZATION


የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከቻይልድፈንድ ጋር በመተባበርበትግራይ ክልል፤ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ ለሚተገብረው ፕሮጀክት የሚከተሉትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝርና ዝርዝር መግለጫ (Specifications):

1. የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ኪት (Dignity Kit): ስለ ዕቃው ብዛት፣ አይነት፣ ጥራት እና የማሸጊያ መስፈርቶች ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተካቷል::

2. ተጨማሪ ምግብ: -

  • RUSF (Ready-to-Use Supplementary Food) / ለመጠቀም ዝግጁ የሆነ የተጨማሪ ምግብ ምርት
  • CSB++ (Corn Soy Blend Plus Plus) / በንጥረ ነገር ይዘቱ የተሻሻለ የበቆሎና የሶያ ቅይጥ:: የንጥረ ነገር ይዘትና ሌሎች መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተካተዋል::

በመሆኑም በመስኩ የተሠማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ

1) በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ

2) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርትፊኬት እና የግብር ከፋይ መለያ TC (TIN)

3) የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማሰረጃ በማቅረብ

ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይቀናት ውስጥ፣ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ቀይት በሚገኘው ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት፣ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡ 30 ሰዓት ባለው የሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: በተጨማሪም፣ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል አድራሻ procurement@tesfab.org በመጠየቅ እና የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በባንክ ገቢ በማድረግ ማግኘት ይቻላል:: ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን ከሰነዱ በማየትና በመሙላት፣ በደብረ ብርሃን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲሁም በመቀሌና አዲስ አበባ በሚገኝው የቻይልድፈንድ ቢሮ ዋናውን እና ኮፒውን ማስገባት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት ይገልፃል::

 

ተጫራቾች የጠቅላላ የጨረታ ዋጋቸውን 1% (አንድ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በ''ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት" ስም አሰርተው ማስያዝ አለባቸው:: ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የመጨረሻው የሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ተዘግቶ፣ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ጨረታውን ለመካፈል በተገኙ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::

 

ማሳሰቢያ፡ - ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው ውጤት አይገደድም::

አድራሻ፡ ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት

ደብረ ብርሃን፣ ቀይት ዋና ጽ/ቤት

 

Save Tender