በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የ2018 ሎቶች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የልደታ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር-001
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ለልደታ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የ2018 ሎቶች ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን ብር 1000
ሎች 2 ቋሚ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን ብር 5000
ሎት 3 የአበባ እና የዛፍ ችግኝ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን ብር 3000 አሸናፈ የሚያቀርበው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ እስከ 60 ቀን ድረስ የዋጋ ለውጥ ማድረግ አይቻልም፤
- በዚህ ጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው በካሽ ከሆነ አንቀበልም፤
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለእያንዳንዳቸው ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ልደታ ጤና ጣቢያ ህንፃ 5ኛ ላይ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሳጥን ውስጥ ኮፒ እና ኦሪጅናል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 ሰአት ይከፈታል ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማህተም ፤ ፊርማ ፤ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ሰነድ መኖር አለበት ፤ ዋጋው የሚሞላበት ሰነድ መስሪያ ቤቱ በሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ መሆን አለበት እና እያንዳንዱ ተጫራች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በገዛው ሎት ልክ ነው ማለትም አንድ ከገዛ አንድ እንጂ በአንድ ሎት 2-3 መወዳደር አይቻልም ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የልደታ ጤና ጣቢያ ከልደታ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ምርታማነት ማሻሻያ ጸበሉ ጎን
የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 0115-58-20-61 ወይም 011 5-58-49-66
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የልደታ ጤና ጣቢያ
