Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline22 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security20000.00
  • opening date2025-07-22 00:00:00
  • Categories Gardening And Landscaping , Flora And Horticulture

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይላይት ሆቴል የተለያዩ የአበባ ዓይነቶች አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T547

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይላይት ሆቴል የተለያዩ የአበባ ዓይነቶች አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በተጠቀሰው አገልግሎት ዘርፍ ላይ ቢያንስ ሦስት (3) ዓመት የሰሩ ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት : TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያላቸውና በዘርፉ እየሰራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T547 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 ( ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል። ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እሰከ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

በስልክ ቁጥር 011 517 8025

ኢ-ሜይል: eskedarya@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

 

Save Tender