በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ከላይ የተሰጡትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ይዘው መቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ) ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ግዥ ከፍል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩኘ አዲስ ማሽን እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው፡፡
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
