የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎት 1 የተማሪ ወንበር እና ጠረጴዛ ጥገና የእጅ ዋጋ 1 ሎት 2 የወንበር እና የጠረጴዛ መስሪያ ማቴርያል እቃ አቅርቦት ግዥ፣ ሎት3 የተማሪዎች የእጅ መታጠቢያ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Gondar Teachers College (የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ጎመትኮ ግ/ፋ/ን/ አስ -2 /718/17
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎት 1 የተማሪ ወንበር እና ጠረጴዛ ጥገና የእጅ ዋጋ 1 ሎት 2 የወንበር እና የጠረጴዛ መስሪያ ማቴርያል እቃ አቅርቦት ግዥ፣ ሎት3 የተማሪዎች የእጅ መታጠቢያ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የሚመለከተው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው።
- የግዥው የብር መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ለዚህም ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከነ - 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከዚህ በፊት በተሰጣቸው የእቃ አቅርቦት ወይም አገልግሎቶች ችግር ኖሮባቸው በየደረጃው በተቀመጠው አግባብ ባለውና በሚመለከተው አካል እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የሚሰሩ ስራዎችን አይነትና መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ሎት 1 እና 2 ከ06/10/2017 ዓ/ም እስከ 25 /10/2017 ዓ.ም ፤ ሎት3 ከ06/10/2017 ዓ/ም እስከ 2/11/2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ወይም 19 መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠ/ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማርኛ የተተረጎመ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለበት። በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ በውስጥ ገቢ ደረሰኝ መቁረጥ አለበት ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በጎንደር መም/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰአት ሎት1 እና ሎት2 በ26/10/17 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሎት3 በ3/11/2017 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎ/መ/ት/ኮ ቢሮ ቁጥር G-01 በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰአት ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን ቀኑ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኮሌጁ ቫት ሰብሳቢ በመሆኑ የቫት ሂሳብን 7.5% ቆርጠን የምናስቀር መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጎ/መ/ት/ኮሌጅ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
