የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተሽከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጎማዎች ከነካላማደሪያና ፍላፕ፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች እና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቐለ ሪጅን ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር MKREU-002/2017
የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተሽከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጎማዎች ከነካላማደሪያና ፍላፕ፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች እና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ይሆናል፡-
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት መጠን |
ብዛት |
|
ሎት 1 |
የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማዎች ከነካላማዳሪና ፍላፕ |
158 |
|
ሎት 2 |
የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች (ፊልትሮዎች፤ የእግር ቤሪንግ እና የፍሬን ሸራዎችን ፓዶች) |
ዝርዝሩ ላይ ቀርቧል |
|
ሎት 3 |
የተለያዩ የተሽከርካሪ ባትሪዎች |
80 |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስከር ወረቀት፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ማስረጃ ያለው መሆን አለበት፤
- በጨረታው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣ መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው እና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ሓወልቲ ክ/ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ሳፕላይቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በየሎቱ ሆኖ ብር 100,000.00 (መቶ ሺ ብር) ለሎት 1፣ ለሎት2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) እንዲሁም ለሎት 3 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥሩ MKREU-002/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 304 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰአት በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251342406712 መደወል ይችላሉ ፡፡
የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
