Tender Detail

Tender Details


የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሞተር ሳይክሎች የእርሻ መሳሪያዎች የመኪና ተመላሽ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 09

 

የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሞተር ሳይክሎች የእርሻ መሳሪያዎች የመኪና ተመላሽ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታዉ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።

  1. ተጫራቾች ከዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10000 /አስር ሺ ብር/ ከባንክ በተረጋጠ ቼክ /ሲፕኦ/ በማያያዝ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በ11ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

1ኛ. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፣

2ኛ. ወረዳዉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

3ኛ. በተራ ቁጥር 1. ከዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ቢባልም ማንኛውም ግለሰብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

በተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113302079 / ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

 

በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ወልቂጤ

 

Save Tender