የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ህክምና ኮሌጅ አገልግሎት ላይ የማይውሉ የአልሙንየም ስክራፕ፤ ቁርጥራጭ ብረታብረት፣ አገልግለው የተመለሱ የተሸርካሪ መለዋወጫዎች ፤ እስከራፕ የተደረገ ማሽን እንዲሁም ባለ 5 /አምስት/ እና 10 /አስር / ሊትር ጀሪካኖች እና ያለቁ የፕሪንተር ካርትሬጆችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
St. Paul's Hospital Millennium Medical College (የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ህክምና ኮሌጅ)
የሚወገዱ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ህክምና ኮሌጅ አገልግሎት ላይ የማይውሉ የአልሙንየም ስክራፕ፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፣ አገልግለው የተመለሱ የተሸርካሪ መለዋወጫዎች ፤ እስከራፕ የተደረገ ማሽን እንዲሁም ባለ 5 /አምስት/ እና 10 /አስር / ሊትር ጀሪካኖች እና ያለቁ የፕሪንተር ካርትሬጆችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ማንኛውም ህጋዊ ግለሰብ ወይም ድርጅት ለመወዳደር ፍቃደኛ የሆነ
- በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሰው የመነሻ ዋጋ በላይ ዋጋ የሚያቀርብ
- ተጫቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺ ብር / በባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፍል በአስተዳደር ህንጻ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር 97 እስከ 11፡00 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በአሸናፊነት የሚመረጠው ተጫራች ንብረቱን በራሱ ተሽከርካሪና የትራንስፖርት ወጪ የማንሳት ኃላፊነት ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆን ተጫራች ውል ተዋውሎ የሚወገዱ ንብረቶችን ውል ከተዋወለበት ቀን አንስቶ በሰባት የስራ ቀናት ውስጥ አንስቶ መውሰድ ግደታ አለበት፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሰው የኪሎ መነሻ ዋጋ በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊው የሚለየው ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች ነው፡፡
- ውድድሩ የሚደረገው በነጠላ ውድድር ነው፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ አስራ አምስተኛው ቀን ላይ 8፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ መሰረት አስፈላጊ ሰነዶችን አያይዘው እና ዋጋውን ሞልተው በማቅረብ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ፖስታ የውጨኛው ክፍል ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወገዱ ንብረቶችን በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0112763531 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ህክምና ኮሌጅ
