የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን (ማሸነሪዎችን) እና ኦክስጅን ከነትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Hawela Tula General Hospital (የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን (ማሸነሪዎችን) እና ኦክስጅን ከነትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በሆስፒታሉ ስም ማሰራት አለባችሁ፡፡
የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ብሎ በፖስታ ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል:: ሲፒኦ ብቻ ያለበት በፖስታ ለብቻ መኖር አለበት፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የስራ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛ ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል በግዥና ክፍያ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለዉ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት እያስተጓጉልም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0916836497/0924302087
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ
የሀዌላ ቱላ አጠቃላይ ሆስፒታል
