የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በአዳማ ከተማ በሚገኝ ለኮንስትራክሽን ግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ኤጀንሲዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ጋር ውል ለመግባት ይፈልጋል፡፡
Oromia Construction Corporation (OCC) (የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB/OCC 044/2025
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በአዳማ ከተማ በሚገኝ ለኮንስትራክሽን ግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ወይም ኤጀንሲዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ጋር ውል ለመግባት ይፈልጋል፡፡
በመስኩ የተሰማሩ የአገልገሎቱ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ ግብር የተገበረበትና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- በአገልግሎት አቅራቢነት ምዝገባ ከሚመለከታቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የቫት ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ጊዜው ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ መመሪያ (ሰነድ) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ 1ኛ ፎቅ በመግዛት ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ወይም በዕለቱ በግንባር በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ "CPO" ማስያዝ አለባቸው::
- የጨረታ ሠነድ አርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተለይቶ ለየብቻ ታሽጎ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውም ለብቻው ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማሻሻል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖረሽን 1ኛ ፎቅ ፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011-439-05-86/439-11-10
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
