Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-23 00:00:00
  • Categories Vehicle Battery

ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ለነባር ትራከር እና ሬኖ ከባድ ተሽከርካሪ የሚውል 9*11 ዋና ሸራ እና 9*11 የፕላስቲክ ሸራ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።


 

ለነባር ትራከርና ሬኖ ከባድ ተሽከርካሪ የሚውል ዋና ሽራ እና 

የኘላስቲክ ሸራ የጨረታ መመሪያና ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ ት /ድ/አቅ/014/17

 

ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ለነባር ትራከር እና ሬኖ ከባድ ተሽከርካሪ የሚውል 9*11 ዋና ሸራ እና 9*11 የፕላስቲክ ሸራ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።

1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. በገንዘብ ሚኒስቴር (ንብረት አስተዳደር) በመንግስት ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤

5. ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅ/ፋ/ማ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ፤ በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ እና ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ። በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ/ ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።

11. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ያሸነፈበትን ጥቅል ዋጋ ብር 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማል፤

12. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀየር ብዛት በ20% ለመጨመር/ለመቀነስ መብት አለው።

13. ጨረታው ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።

14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011 439 00 75/ 011 439 10 27 መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

 

ዕለት ደራሽ የዕዳርታ ትራንስፖርት ድርጅት

 

Save Tender