Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0967441304
  • Website
  • Deadline16 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-16 00:00:00
  • Categories Forest And Tree Sales

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በአካባቢ ጥበቃና ደን ጽ/ቤት አስተባባሪነት በጌታ ወረዳ ቀቡል ከተማና በቀቡል ገጠር ቀበሌዎች በጋራ የሚገኝ የሰው ሠራሽ የማህበረሰብ ደን (ነጭ የባህር ዛፍ) አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በአካባቢ ጥበቃና ደን ጽ/ቤት አስተባባሪነት በጌታ ወረዳ ቀቡል ከተማና በቀቡል ገጠር ቀበሌዎች በጋራ የሚገኝ የሰው ሠራሽ የማህበረሰብ ደን (ነጭ የባህር ዛፍ) አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ደኖቹ ውስጥ ያለው የባህር ዛፍ አይነት ወራጅ ፣ ማገር ፣ ተሸጋጋሪ ፣ የፖል እንጨት እና ጨፈቃ… ወዘተ ያካተተ መሆኑን እየገለፅን ያለው የደኑ ስፋት ደግሞ 53.99 ሄ/ር ነው:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረው መስፈርት የምታሟሉ በጨረታ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት ዐሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

  2. ተጫራቶች በእንጨት አቅርቦት (ሽያጭ) ወይም በሌሎችም ስራ ዘርፍ ላይ የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው::

  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ::

  4. ጨረታው ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ለወደፊቱ ከመንግስት መስሪያ ቤት የሚወጡ ጨረታዎች እንዳይሳተፉ እንደሚደርግና የጨረታ | ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡

  5. ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም

  6. ተጫራቾች ደኑ መጎብኘታቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ከቀቡል ገጠር/ ከቀቡል ከተማ ቀበሌዎች የማህበረ ሰብ ደን ከቀበሌው ሊቀ -መንበር (ስራ አስኪያጅ ) አፅፈው ከጨረታው ሰነድ አብረው በሚታይ መልኩ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት።

  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 91.000 (ዘጠና አንድ ሺህ ) ብር ሲፒኦ እውቅና ባለው ባንክ በጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።

  9. የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊነት ማስታወቂያ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ለተሸናፊዎች ይመለሳል፡፡

  10. ጨረታውን መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛ ተከታታይ ቀን 6፡00 ድረስ የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የቀቡል ከተማና ቀቡል ገጠር የማህበረ ሰብ ደን ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡

  11. ጨረታውን በእንድ እናት ፖስታ አንድ ኦርጅናል ሁለት ቅጂ በድርጅቱ ባለስልጣን የተፈረመበት እና ማህተም ተደርጎበት እስከ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን የሚመለከተው አካል በማሳወቅ መጨመር አለበት።

  12. የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛ ቀን 8፡00 ሰዓት የጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ታሽጎ በእዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፣ ባይገኙም ይከፈታል፡፡

  13. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ በኋላ በ7 ቀን ውስጥ 10 ፐርሰንት ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት ::

ማሳሰቢያ፡-

  1. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

  2. የጨረታው አሸናፊ ከተለየና ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ ለ9o ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንጨቱ ሙሉ በሙሉ ቆርጦ የሚጨርስ ተጫራች መሆን አለበት።

  3. 15ኛ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሌላኛው ቀን እላይ በተገለጸው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0967 441304/ 0961178110 እና 0943260350 መደወል ይችላሉ።

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender