የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ለራሱ እና በስሩ ላሉ ፑል መ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1- የጽሕፈት መሳሪያዎች ፤ ሎት 2- ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች (እስካነር)፤ ሎት 3- ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና ሎት 4- ህትመት ፤ ሎት 5- የፅዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
FEDERAL TAX APPEAL COMMISSION (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ለራሱ እና በስሩ ላሉ ፑል መ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1- የጽሕፈት መሳሪያዎች ፤ ሎት 2- ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች (እስካነር)፤ ሎት 3- ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና ሎት 4- ህትመት ፤ ሎት 5- የፅዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ /eg-p/ ማያያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1፤ የፅህፈት መሳሪያዎች 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት 2፤ ፕላንት ማሽነሪና መሳሪያዎች (ስካነር) 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት 3፤ ፕላንትና ማሽነሪ ጥገና 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለሎት 4፤ ህትመት 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 5፤ የፅዳት ዕቃዎች 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ cpo ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ቴክኒክ እና ፋይናንስ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ01 /አንድ/ ኮፒ ጋር በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል። ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡30 ተዘግቶ በዛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተወዳዳሪዎች የሚያስገቡትን ደረጃቸውን የጠበቁ እቃዎችን ናሙና በተዘጋጀው ክፍል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-558 28 51 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን
