Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-8340-636
  • Website
  • Deadline14 Mar 2025, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ ዞን ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና የመኪና ጎማዎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)


 

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 11/2017

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ ዞን ከተማና ወረዳ የሚገኙ

  • የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣
  • ሞተር ሳይክሎች፣
  • የመኪና ጎማዎች እና ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የኤጀንሲዉ አድራሻ ፤አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጲያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ጨፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘዉ የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 Floor) ቢሮ ቁጥር-02 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ብቻ ነው::
  3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ መጋቢት 03/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው መጋቢት 04/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

CPO ለማሰራት

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግስት

ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-8340-636

 

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት

ማስወገድ ኤጀንሲ

ፊንፊኔ

 

Save Tender