Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ ጤና ጣቢያ
  • Address የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 893 29 82
  • Website
  • Deadline17 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ የህክምና መሳሪዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ የኮንስትራከሽን እቃዎች የቋሚ ዕቃዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች የጀኔሬተር ግዢ እንዲሁም የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና የሚወገዱ ዕቃዎችን አጫርቶ ለመሸጥ በተጨማሪም የውሃ ሮቶ እጥበትን ጨምሮ ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካ ጤና ጣቢያ


 

የ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ መድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ የህክምና መሳሪዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ የኮንስትራከሽን እቃዎች የቋሚ ዕቃዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች የጀኔሬተር ግዢ እንዲሁም የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና የሚወገዱ ዕቃዎችን አጫርቶ ለመሸጥ በተጨማሪም የውሃ ሮቶ እጥበትን ጨምሮ ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።

በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የሚያገለግል ብር 3000.00 (ሶስት ሺ ብር) በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን በመገኝት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  7. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ 4 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቶች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
  9. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 የስራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል።
  10. አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
  11. የሚወገዱ ዕቃዎችን ለመሸጥ ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩት ቅድመ የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም
  12. ጤና ጣቢያው የአቅርቦት ዝርዝር ስፔስፍኬሽን በሚጠይቁ አቅርቦቶች ላይ ባወጣው መሰረት ተጫራቾች ካታሎግን ጨምሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  13. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር ፡- 011 893 29 82/ 011 667 42 37

 

በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender