የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ልዩ ልዩ የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች፤ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤
- የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫቶችን /Dustbin/፤ የደንብ ልብሶች፤ የተለያዩ ኮምፒዩተሮች እና
- ተዛማጅ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) ስንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሣብ ቁጥር 1064540111215 ገቢ በማድረግ ዲፖዚት ሲልፑን/ Deposit slip ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንፃ አንደኛ ፎቅ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር ክፍል በማቅረብ እና ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ሁለተኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ ንብረት አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም ኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ 200,000.00 ብር CPO (ሲፒኦ) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ብቻ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የመንግስት የሥራ ቀናት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንጻ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜ ፤ እሁድ ወይም የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና /sample/ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 0114-70-93-00/09-12-60-52-36 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
አድራሻ
ሳሪስ በአልትሜት ሞተርስ ገባ ብሱ የቀድሞው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
