በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን ለኢንጌ ከተማ የታንከር ግንባታ፣ የወለጋ ዲሴ ቀበሌ መስመር ዝርጋታ ስራ፣ ቀቻ ቀበሌ የምንጭ ጥገና ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር:- GGWW/022/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን ለኢንጌ ከተማ የታንከር ግንባታ፣ የወለጋ ዲሴ ቀበሌ መስመር ዝርጋታ ስራ፣ ቀቻ ቀበሌ የምንጭ ጥገና ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/WC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች፤
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት፣ ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ/ ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል፤
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር: 011-3-36-01-62/146 ደደውሉ፡፡
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
