የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ሥር በሚገኙ የተለያየ ደረጃ ላላቸው የእንስሳት ክሊኒኮች የህክምና መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን የተወዳደሪዎች መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው ሥር በሚገኙ የተለያየ ደረጃ ላላቸው የእንስሳት ክሊኒኮች የህክምና መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን የተወዳደሪዎች መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተከፈተው ሰንቄ ሂሳብ ባንከ ቁጥር 1064540111215 ገቢ በማድረግ ዲፖዚት ስሊፑን /Deposit slip/ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በማቅረብ እና ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን 2ተኛ ፎቅ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት፣ አስተዳደር አወጋገድ እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም ኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) ብቻ በሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በድርጅቱ ጨረታ ሰነዱ ላይ ብቻ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የመንግሥት የሥራ ቀናት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች- 0114-70-93-00 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡-
ሳሪስ በአልትሜት ሞተርስ ገባ ብሎ የቀድሞ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
