የአፈር ማዳበሪያ ከቡራዩ /ታጠቅ/ በምዕራብ ሸዋ ዞን በቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ሥር ላሉት መሠረታዊ የሕ/ሥራ ማኅበራት ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
የቦሬ ባኮ የገ/ሕ ሥራ ዩኒዬን (ኃ/የተ)
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን (ኃ/የተ) ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል "NPS, NPSB, DAP AS UREA"
የአፈር ማዳበሪያ ከቡራዩ /ታጠቅ/ በምዕራብ ሸዋ ዞን በቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ሥር ላሉት መሠረታዊ የሕ/ሥራ ማኅበራት ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር (አ/ማ) የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው።
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የማጓጓዣ ታሪፍን በኩንታል እና በኪሎ ሜትር መስጠት አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ያላቸውን የመኪና ብዛት እና የመጫን አቅም ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሃያ /20%/ CPO ወይም “Bid Guarantee" ለመጫረት ካቀረበው የማዳበሪያ መጠን ጋር አጣጥሞ ማቅረብ አለበት። የጨረታው ማጣራት እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው ለአሸናፊዎች ግን ከመልካም የሥራ አፈፃፀም ላይ ይታሰብላቸዋል፡፡
- የማራገፊያ ጣብያዎቹን እና የማዳበሪያውን ብዛት የሚገልጽ ሠነድ ባኮ ከተማ ከዩኒዬኑ ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ 3000.00 /ሦስት ሺህ/ ብር በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ4:30 ሰዓት ታሽጎ በ5:00 ሰዓት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታ መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙት ፊት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- በተቀራራቢ ጣቢያዎች ላይ የተጋነነ የዋጋ ልዩነቶችን ለማስታረቅ ሲባል ዩኒዬኑ የራሱን አማራጭ የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
- ዩኒዬኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ዞን የቦሬ ባኮ (ኃ/የተ) የገበሬዎች ሕ/ሥራ ዩኒዬን
ስልክ ቁጥር :- 0942941011 /0920423406 /0917723912/
0576651374
የቦሬ ባኮ የገ/ሕ ሥራ ዩኒዬን (ኃ/የተ)
