የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪዎች ፍላጎት ላላቸው ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
NATIONAL BANK OF ETHIOPIA (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ)
ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ባትሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪዎች ፍላጎት ላላቸው ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም -
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ /ድርጅት/ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጣበት ወቅት ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን መታወቂያ ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በህንፃ ቁጥር 2 ምድር ቤት ላይ በሚገኘው ክፍያና ሒሳብ ማወራረጃ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስም በሂሳብ ቁጥር 7002010800001 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ በህንፃ ቁጥር 2 2ኛ ፎቅ ኢንጅነሪንግ፣ ንብረትና ትራንስፖርት አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለጨረታው መረጃ ማግኘትና የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ ለጎማ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) እና ለባትሪ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ክፍል የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ከጥር 05 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስራ ቀናቶች ጎማና ባትሪዎችን ማየት ይቻላሉ::
- ተጫራቶች ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማ እና ባትሪ የሚገዙበትን ዋጋ ማስረከቢያ ቅፅ ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሙሉ አድራሻውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህንፃ ቁጥር 2 ሁለተኛ ፎቅ ኢንጅነሪንግ፣ ንብረትና ትራንስፖርት አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ለተሽከርካሪ ጎማ እና ባትሪ ጨረታ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0115175193 / 0115175204 ደውሎ መጠየቅ ይችላል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
