Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address የሰሜን ሸዋ ዞን ከአ/አበባ በስተ ሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት ደ/ሃርህን መስመር ላይ ይገኛል : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 011-6 32-01-47
  • Website
  • Deadline21 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ የትምህርት እቃዎች እና የተለያዩ የትምህርት አጋዥ መጽሃፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ የትምህርት እቃዎች እና የተለያዩ የትምህርት አጋዥ መጽሃፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ :-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. እቃዎቹን በአንድ ጊዜ በአይነት፣ በመጠን፣ በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን፣ አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ገ/ኢ/ት/ዋና ጽ/ቤት በመሂ1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የእቃ ግዥ መ/ቤቱን፣ የተጫራቹን ስምና አድራሻ ፣ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከሰአት 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከሰዓት 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  6. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል፤
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ያወዳድራል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ንብረት ክፍል ድረስ በመውሰድ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፤
  11. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደ/ብርሃን መስመር ላይ ነው፡፡
  14. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-01-47 ወይም 011-6 32-03-04 ደውለው ይጠይቁ።

 

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender