Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ
  • Address , Phone: 0222115890
  • Website
  • Deadline20 Jan 2025, 10:14 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት በአዳማ እና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የአዳማ


 

የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  አገ 09/2017

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት በአዳማ እና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል::

  1. አገልግሎቱ የሚቀርበው በአዳማ እና በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል::
  2. ተጫራቾች በትራንስፖርት የስራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ ገጽ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት እና የቫት ሰርተፊኬት ያላቸው እንዲሁም የስራ ግብር የከፈሉና ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዳማ የቀድሞው ጅንአድ ፊት ለፊት የሚገኘው የገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 በፊት ለጨረታው የሚያስፈልግ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ በቅ/ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው:: በመሆኑም የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  5. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:15 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ፣ ፋይናንስ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ስከበሪያ እንደተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ፤ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት (MINISTRY OF REVENUE ADAMA BRANCH) ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: +251-22-211-40-10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት

 

Save Tender