በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለተንታ ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የእንስሳት መድሃኒት እና የእንስሳት ህክምና መሳሪያ በ2017 የመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፦ 02/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለተንታ ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የእንስሳት መድሃኒት እና የእንስሳት ህክምና መሳሪያ በ2017 የመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የእንስሳት መድሃኒት፣
- ሎት 2. የእንስሳት የህክምና መሳሪያ፣
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን።
- ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ከተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰአት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃ አቅርቦት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም 4:00 ሰአት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡15 ሰአት በይፋ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው፣ ግልፅና የማያሻማ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ የሚታሸግበትን ፖስታ ጨምሮ በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ገፆች ላይ የጨረታውን ዓይነት፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾት አንድ ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኦርጅናልና ኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ግዥው ኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ በመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤታችን አሸናፊውን የሚመርጠው በሎት ጥቅል ዋጋ ድምር ዝቅተኛ የሞላውን አሸናፊ ይሆናል። ስለሆነም በሎት ከተገለጸው የእቃ ዝርዝር ውስጥ ለይቶ መሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ ማንኛውንም ወጭ ችሎ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉት እቃ ገቢ በሚሆንበት ጊዜ ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ እና የታሸጉ እቃዎች ተፈተውና ታይተው ችግር ቢኖርባቸው የማንቀበል መሆኑን እና የሚያቀርባቸው እቃዎች ጥራት ያላቸው መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- መ/ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ የተጠየቀውን እቃ ብዛት 20% ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበአላት ቀን፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰአት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-441-05-73 ወይም 033-441 02-67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
