Tender Detail

Tender Details

  • Company የደገሌ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር
  • Address ሙዱላ ከተማ መነሐሪያ አካባቢ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-10-85-17-95
  • Website
  • Deadline02 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

የደገሌ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2017 ዓ.ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኛው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማራገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ ፣ በልግና ለመኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

የደገሌ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር


የደረቅ  ጭነት  ማመላለሻ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  001/2017 ዓ.ም

 

የደገሌ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2017 ዓ.ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኛው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማራገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ ፣ በልግና ለመኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተስልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት :-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና ህጋዊ ሰውነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ ተቋም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የተሽካርካርዎቹን ኢንሹራንስ መድን ዋስትና የዘመኑን ማቅረብ የሚችል፣
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል ይመረጣል፡፡
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር /50,000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን /የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም፣ የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የደገሌ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር ዋና ጽ/ቤት ሙዱላ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  8. የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበር ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ጊዜ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  10. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡-  ሙዱላ  ከተማ  መነሐሪያ  አካባቢ

ስልክ ቁጥር :-  09-10-85-17-95/09-28-76-79-61

 

የደገሌ  ገበሬዎች  ኅብረት  ሥራ  ማህበር

Save Tender