የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መ/ቤት ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው የሆስፒታል የዱቤ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከጨረታው አሸናፊ ሆስፒታል ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ የዱቤ አገልግሎት ግዥ ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/19/SIG/2017
- የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋናው መ/ቤት ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው የሆስፒታል የዱቤ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከጨረታው አሸናፊ ሆስፒታል ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ የዱቤ አገልግሎት ግዥ ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቶች ሕጋዊ የ2016/17 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ጋፍ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/ አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት
ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 50 04 17 ወይም 011 5 51 62 71
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
- ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
