የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ለያዝነው 2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አነስተኛ የእርሻ መገልገያዎች፣ የጽዳት ቁሳቁሶች (እቃዎች)፣ አነስተኛ የላብራቶሪ መገልገያ እቃዎች፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎች፣ የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በመስኩ ንግድ ፍቃድ ካላቸውን የዘመኑን ግብር ከከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑና የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ከሚችሉ ማህበራት/ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡-01/2017 ዓ.ም
የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ለያዝነው 2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አነስተኛ የእርሻ መገልገያዎች፣ የጽዳት ቁሳቁሶች (እቃዎች)፣ አነስተኛ የላብራቶሪ መገልገያ እቃዎች፣ የላብራቶሪ ኬሚካሎች፣ የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒቶችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በመስኩ ንግድ ፍቃድ ካላቸውን የዘመኑን ግብር ከከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑና የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ከሚችሉ ማህበራት/ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ የማይመለስ 800.00 (ስምንት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካይ ተፈርሞ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች ማሸግ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር ያቀረቡትን የጠቅላላ ግዥ ዋጋ ድምር 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በጋራ በተገኙበት በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋጀው በአማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ ይሆናል፡፡
- ማዕከሉ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ዕለት በዝግ የስራ ቀናት ወይም በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው የመክፈቻ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ስልክ ቁጥር :- 011-2-37-02-92/011-2-37-24-42 ፋክስ 011-2-37-03-77
ሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል
