Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printer And Photocopy Machine

ማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በበጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የመንጃ ፈቃድ ማተሚያ ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

 

ማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በበጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የመንጃ ፈቃድ ማተሚያ ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ  መሰረት  በጨረታው  ለመሳተፍ  የሚፈልጉ  ተጫራቾች

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ
  4. የቲን ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት ያለው
  5. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው የኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጂናል/ወይም/ ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለተጫራቾች የንግድ ፊቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና CV ኮፒ ተብሎ በተገለፁት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦሪጅናል / ሆኖ ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በፊት ብቻ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ይከፈታል፡ ፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል። ማንኛውም የተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንከ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
  11. ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈለግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢ/ዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0113659360 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

የቢሮው አድራሻ ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡

 

ማዕከላዊ  ኢትዮጵያ  ክልል  መንግስት  ትራንስፖርትና  መንገድ  ልማት  ቢሮ

 

Save Tender