Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
  • Address ከሜከሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 25111508685
  • Website
  • Deadline21 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printed Advertising Materials

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ እስቲከሮች አለሙኒየም ላይ ለማስለጠፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ እስቲከሮች አለሙኒየም ላይ ለማስለጠፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም  ተጫራቾች :-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው::
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ከላይ የተሰጡት እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ከዚህ በፊት ከግልም ሆነ ከመንግስት የሰራበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  6. የተፈለገው እስቲከር ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. 3ኤም ማይክሮ ፕሪዝማቲክ ሪፍለከቲቭ እስቲከር ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን አራት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
  11. ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8:00 (በስምንት ሰዓት) ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

አድራሻ ፡- ከሜከሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ

 

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዲስ ማሽንና እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ

Save Tender