በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ቢሮው ለኢኮቴ ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ አድቫንስ ስልጠና ለመስጠት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ቢሮው ለኢኮቴ ባለሙያዎች ደረጃውን የጠበቀ አድቫንስ ስልጠና ለመስጠት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ ያላቸው
- በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘበ እና በህግ ያልተገደበ
- ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ በቢሮው የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮው የግዥ ፋይ/ ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይቻላሉ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለየብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና (ኦርጂናል) ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ምሳሌ ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒከ የጨረታ ሰነድ በሆነው በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብለው በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብለው በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው/ኦሪጅናል ሆነ ኮፒ ኤንቬሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ብቻ ሰነዱ የሚሸጥ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 15ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ጋራንቲ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የፅህፈት መሳሪያ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል።
አድራሻ ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
