በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሥር የሚገኘው ሁላ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሁላ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሥር የሚገኘው ሁላ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን
ማለትም
1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ዝርዝር
- ላፕቶፓች
- ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች
- ፕሪንተሮች
- ፍላሾች
በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቾቹ የዘመኑን ግብር በመገበር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- ተጫራቾቹ የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ (BID security) CPO በሁላ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ስም በማሰራት ከሚያቀርበው ዋጋ በባንከ 2% ማቅረብ የሚችሉ፣
- የመወዳደሪያ ሠነዱን 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሁላ ኮ/ኢ/ኮሌጅ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ በስራ ቀናት ይሆናል፣
- ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዶችን በአርጅናልና በኮፒ ተደርጎ በማሸግ በሁለት ፖስታዎች ላይ
- የድርጅቱን አድራሻ የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ስምና ፊርማ በማኖር በተለያዩ ፖስታዎች የታሸጉትን ኦርጅናልና ኮፒ ሁለቱም ፖስታዎችን በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን በሁላ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ቢሮ ቁ.1 በአካል በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ4፡00 ሰዓት በማስገባት ማሳሸግ ይኖርባችዋል።
- ጨረታውን በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፣
- ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ጨረታ አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡-
09 16 30 76 49
09 26 58 63 41
በሲዳማ ብ/ክ/ መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሁላ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
