እድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የ/ኅ/ሥራ ዩኒየን ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል NPSB,Nps እና UREA የአፈር ማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሰራጨት ሕጋዊ የሆኑ የሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አድገዩ/001/2017ዓ.ም
እድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የ/ኅ/ሥራ ዩኒየን ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል NPSB,Nps እና UREA የአፈር ማዳበሪያ በጉራጌ ዞን ላሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማሰራጨት ሕጋዊ የሆኑ የሀገር ውስጥ ደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች ማሟላት የሚችል በዘርፉ የተሰማራ ማንኛውም የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅት በጨረታው መሳተፍ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዩኑየኑ ፅ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 400,000 /አራት መቶ ሺ ብር/ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዩኑየኑ ሂሳብ ክፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱን ሕጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ዩንየኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራች ድርጅት ከዚህ በፊት በአድማስ ኃላ/የተ/የግ/ኅ/ሥራ ዩኒየን የወጡ ጨረታዎችን ካሸነፈ በኋላ ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ መሆን አለበት፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር፡- 0113301519/0936780943/0912775381 በመጠቀም ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ኅ/ሥራ ዩኒየን
ጉራጌ ዞን ወልቂጤ
