የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የ2016 በጀት ዓመት ሂሳብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)
የኦዲተ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የ2016 በጀት ዓመት ሂሳብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- የኮርፖሬሽኑን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax Identification Number (TIN) ያለው::
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ከደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የሂሳብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙኃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ድረስ ድረስ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ሁለት መቶ ብር ከፍሎ ከኮርፖሬሽኑ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ፣ የዋጋ መወዳደሪያ ሰነድ " እና “ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ በማስያዝ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 29 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 29 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፦ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር-058-218-02-731 በመደወል ወደም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 (058-218-05-60) በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
ባህር ዳር - ኢትዮጵያ
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን
